top of page
Search

ደቡብ ሱዳን ከአፍሪካ ሕብረት አባልነት ታገደች።

  • Ethio-Daily ኢትዮ- ወቅታዊ
  • Jun 22, 2020
  • 1 min read

ree

ሕብረቱ ደቡብ ሱዳንን ያገደው አገሪቱ ለአፍሪካ ሕብረት መክፈል ያለባትን ዓመታዊ መዋጮ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት መክፈል ባለመቻሏ መሆኑን ሱዳን ትሪቡን ዘግቧል።

በኢትዮጵያ የሚገኙት የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ባሳለፍነው ሳምንት አፍሪካ ሕብረት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ ለመካፈል ወደ ቦታው ቢያመሩም በጸጥታ ሃይሎች ስብሰባውን መካፈል እንደማይችሉ ተነግሯቸው መመለሳቸውንም ዘገባው ጠቁሟል።

ደቡብ ሱዳን ለአፍሪካ ሕብረት መክፈል የነበረባት ከ9 ሚሊዮን ዶላር በላይ እዳ ያለባት ሲሆን ይሄንን ባለማድረጓ አፍሪካ ሕብረት የደቡብ ሱዳን የአፍሪካ ሕብረት አባልነትን ለጊዜው ማገዱ ተገልጿል። የአፍሪካ ሕብረት ከውጭ ተጽዕኖ ለመላቀቅ በሚል ከ2 ዓመት በፊት ባጸደቀው መመሪያ መሰረት ማንኛውም የአፍሪካ ህብረት አባል አገራት መክፈል ካለበት ዓመታዊ ክፍያ ላይ ከ50 በመቶ በላይ ካልከፈለ ከ6 ወር አስከ 2 ዓመት ድረስ ከአባልነት እንዲታገዱ ይደነግጋል። ደቡብ ሱዳን እንደ ጎርጎሮሲያዊያን ዘመን አቆጣጠር በ2011 በህዝበ ውሳኔ ከሱዳን ራሷን የቻለች አገር ብትሆንም ነጻነቷን ባገኘች በሁለት ዓመቱ ደግሞ እስከ አሁን ድረስ በዘለቀው እርስበርስ ጦርነት ውስጥ ትገኛለች

 
 
 

Recent Posts

See All
የላብራቶሪ ምርመራ

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3238 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።...

 
 
 

Comments


Post: Blog2_Post

Subscribe Form

Thanks for submitting!

+251947452470

©2020 by Ethio-Daily ኢትዮ- ወቅታዊ. Proudly created with Wix.com

bottom of page