ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቀዳዳ የተሰራላቸው ማስኮችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ አገደች።
- Ethio-Daily ኢትዮ- ወቅታዊ
- Jun 22, 2020
- 1 min read
ኢትዮጵያ የመተንፈሻ ቀዳዳ የተሰራላቸው ማስኮችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ አገደች።
የኢትዮጲያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል በሚል ጥቅም ላይ ከሚውሉ ማስኮች ውስጥ ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተሰራላቸው ማስኮችን ወደ ሀገር እንዳይገቡ ትዕዛዝ ማስተላፉን አስታውቋል፡፡
ባስልጣኑ ከዚህ ቀደም ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ማስኮች የቫይረሱን ስርጭት ለመጨመር አስተዋፆ አላቸው በሚል ህብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው ማስታወቁ ይታወሳል፡፡
ነገር ግን ባለስልጣኑ ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ህብረተሰቡ እነዚህን ማስኮች ከመጠቀም አልተቆጠበም እና ምን አይነት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው ሲል ኢትዮ ኤፍ ኤም ተቋሙን ጠይቋል፡፡ በባለስልጠኑ የመድሀኒት ምዝገበ እና ፍቃድ ዳይሬክተር አቶ አብደላ ቃሰው እነዚህ ቫልቭ ወይም የመተንፈሻ ቀዳዳ የተገጠመላቸው ማስኮችን ቫይረሱን ለመከላከል በሚል ዓላማ እናስገባ ለሚሉ ሰዎችም ሆነ ሀገር ውስጥ ለማምረት ፍቃድ ለሚጠይቁ ሰዎች ፈቃድ መስጠት አቁመናል ብለዋል፡፡ በተጨማሪም ቫይረሱን ለመከላል በሚል ዓላማ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገቡም ለጉምሩክ ኮሚሽን ደብዳቤ መፃፉን ነግረውናል፡፡ እነዚህ ማስኮች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ሲደረግ የተሰሩበት ዓላማ በሽታውን ለመከላከል በሚል ባለመሆኑ እና ማስኮቹ በተገጠመላቸው የመተንፈሻ ቀዳዳ አማካኝነት ቫይረሱን ከመከላከል ይልቅ ለስርጭቱ ከፍተኛ አስተዋፆ ስለሚያደርጉ ማህበረሰቡ ማስኩን ከመጠቀም እንዲቆጠብ አሰጠንቅቀዋል፡፡
Comments