top of page
Search

የላብራቶሪ ምርመራ

  • Ethio-Daily ኢትዮ- ወቅታዊ
  • Jun 22, 2020
  • 1 min read

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3238 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ ሰላሳ አንድ (131) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡


በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 4663 ደርሷል።


ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 26 (10 ከጤና ተቋም እና 16 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን አንድ ናሙና ከማህበረሰብ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ሰባ አምስት (75) ደርሷል፡፡


በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማንን ጥልቅ ሀዘን እየገለጽን ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እንመኛለን፡፡


በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰማንያ አራት (84) ሰዎች (79 ሰዎች ከ አዲስ አበባ፣ 2ሰዎች ከኦሮሚያ፣ 2 ሰዎች ከትግራይ እና 1 ሰው ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1297 ነው።

 
 
 

Recent Posts

See All

Comments


Post: Blog2_Post

Subscribe Form

Thanks for submitting!

+251947452470

©2020 by Ethio-Daily ኢትዮ- ወቅታዊ. Proudly created with Wix.com

bottom of page